የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር

  1. በዚህ አዋጅ አንቀፅ 11መሰረት ለተቆጣጣሪው ባለስልጣን መቅረብ ከሚገባቸው በስተቀር ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮችን ይወስናል፣
  2. የድርጅቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ይቀጥራል፤ ደሞዝና አበሉን ይወስናል፤ያሰናብታል፣
  3. ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪጅ ተጠሪ ሆኑ የሥራ ሃላፊዎችን ቅጥር፣ ምደባ እና ስንብት፣ ደሞዝና አበል ያጸድቃል፤
  4. የድርጅቱን የሥራ ፕሮግራም፣ በጀትና የውስጥ ደንብ ያፀድቃል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤
  5. የድርጅቱን የረጅም ጊዜ ብድሮችና ክሬዲቶች ያፀድቃል፤
  6. በድርጅቱ ህልውና ላይ ወሳኝነት የሌላቸውን ቋሚ ንብረቶች ሽያጭ ያፀድቃል፤
  7. የድርጅቱ ሂሳቦችና ንብረቶች በአግባቡ መያዛቸውን ያረጋግጣል፤
  8. ለድርጅቱ ኦዲተሮች የድርጅቱን የሂሳብ መዝገቦችለተቆጣጣሪው ባለስልጣን ደግሞ ስለ ድርጅቱ ስራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርትና የሂሳብ መግለጫዎችን ያቀርባል፤
  9. የድርጅቱ ካፒታል እንዲጨምርወይም እንዲቀንስ ለተቆጣጣሪው ባለስልጣን ሐሳብ ያቀርባል፡፡

Successfully subscribe !
Already subscribe with this email !