...

ኮርፖሬሽኑ ለሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ተሳትፎ እና ድጋፉ እውቅና ተሰጠው

ቀን: Aug 4, 2025

‎‎ የግብርና ሚኒስቴር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን  እና ግሪን ዌቭ አሊያንስ ሀምሌ 13 ቀን 2017 . በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ባዘጋጁት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መረሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተሳታፊ በመሆን የበኩሉን ድጋፍ አደረገ።

‎‎በዚህ ወቅትም ኮርፖሬሽኑ ላለፉት 6 ተከታታይ ዓመታት  አገራዊ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርን በመደገፍ ላደረገው አስተዋጽኦ  እውቅና ተሰጥቶታል።

‎‎ ኮርፖሬሽኑ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል

...

ኮርፖሬሽኑ የልህቀት ስትራቴጂውን ለማሳከት በሚያስችል አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

ቀን: Aug 4, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራሮች 2017 በጀት አመት የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ትኩረት በማድረግ ገመገሙ።

‎‎በግምገማቸው  ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ ባደረጋቸው የሪፎርም ተግባራትና ፕሮጀክቶች የተመሩበት አግባብ ለተመዘገበው አመርቂ ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ተገልጿል።

‎‎በተጨማሪም በኮርፖሬሽኑ   ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት 2017 በጀት አመት አፈጻጸሞች በቀጣይ አመታት  የተቀመጡ የልህቀት   ጉዞ መዳራሻ ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ መሆናቸው ተገምግሟል።

...

‎ኮርፖሬሽኑ ሁለተኛ ዙር የፊዩውቸር ፕሮጀክት ማናጀሮችን አስመረቀ

ቀን: Aug 4, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 26 የፊውቸር ፕሮጀክት ማናጀሮችን አስመረቀ።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ  ንግግር ያደረጉት  የኮርፖሬሽኑ  ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ

...

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ኮርፖሬሽኑ በሚገነባው ፕሮጀክት ውስጥ ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

ቀን: Aug 4, 2025

‎‎የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሀ ግብ

...

ኮርፖሬሽኑ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር  በመተባበር የቢዝነስ ፎረም አዘጋጀ

ቀን: May 14, 2023

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአፍሪካ ሃገራት መካከል የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማሳደግ የሚያግዝ የምክክር መድረክ ስኬታማ በሆነ መልኩ አካሄደ፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ጉዳዮች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደውን የምክክር መድረክ ሲከፍቱ እንደተናገሩት በአፍሪካ ሃገራት መካከል ዘርፈ-ብዙ የትብብር ማዕቀፍ ለመመስረት የምክክር መድረኩ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑን የማኔጅመንት ቦርድ በሰብሳቢነት የሚመሩት ኢንጂነሯ እንደተናገሩት በአፍሪካ ከመሰረተ ልማት አውታር ግንባታ አንጻር አፍሪካ ያላትን የታመቀ የገበያ ዕድል ለመጠቀም ሀገራት በዓቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በልምድ ልውውጥ ዘርፎች በጋራ መስራት ይገባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የአፍሪካን ሁለንተናዊ ለውጥ ዕውን ለማድረግ ይቻል ዘንድ ከአፍሪካ ወንድምና እህት ሀገራት ጋር በጋራ ለመስራት ከማንኛውም ጊዜ በላቀ ደረጃ ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ደረጃቸውን የጠበቁ የግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን እንደተመሰረተ የተናገሩት ሚኒስትሯ ተቋሙ ወደ ፊት ምህንድስና ዲዛይንን፣ የፕሮጀክት ሥራ አመራርን እና ፕሮጀክት አተገባበርን በሚመለከት የምክክር መድረኩን በሚገባ ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡
የኢ.ኮ.ሥ.ኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ኮርፖሬሽኑን በሚመለከት ለምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በሦስት የግንባታ ድርጅቶች ጥምረት የተቋቋመው ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችና በውጭ ሀገር ከ100 በላይ የግንባታ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ ከ20 ሺህ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተቋሙ ከግንባታ ሥራዎች በተጨማሪ በፕሮጀክት ዲዛይንና ሥራ አመራር አገልግሎት፣ በግንባታ ግብዓት ማምረትና በግንባታ ላይ በሚያተኩሩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ 
ኮርፖሬሽኑ የአፍሪካ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን በመገንባት ረገድ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋር በሽርክናም ሆነ በሌሎች አማራጮች  በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት አለው ብለዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የአፍሪካ የኢንጂነሮች ድርጅቶች ፌደሬሽን ፕሬዚደንት ዶክተር ካዛዋንዲ ፓፒያስ ደደኪን ጨምሮ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ከቡሩንዲ፣ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ከቻድ፣ ከኡጋንዳ፣ ከጂቢቲ፣ ከኢኩዋቶሪያል ጊኒ እና ከታንዛንያ ኢምባሲዎች የተወከሉ ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል፡፡              

 

...

የዚምባቡዌ የልዑካን ቡድን የኮርፖሬሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

ቀን: May 14, 2023

የዚምባቡዌ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ማምረቻ ማዕከልን፣ በተገጣጣሚ ህንፃ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የ5 ሺህ ቤቶች ግንባታንና በቅርቡ የተጠናቀቀውን የኮንስትራክሽን ሙያተኞች ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንዳሉት ኮርፖሬሽኑ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የገበያ አድማሱን ለማስፋት በርካታ ሥራዎችን በሚሰራበትና የኢንተርናሽናሌይዜሽን ሪፎርምን ተግባራዊ እያደረግንበት ባለበት ወቅት የተደረገ የልምድ ልውውጥ ስለሆነ ጠቃሚ ልምዶችን የልዑክ ቡድኑ ከኮርፖሬሽኑ እንደሚያገኝ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ግድቦች፣ የመስኖ እና የውሀ አቅርቦት ሥራዎችን፣ የህንፃና ቤቶች ግንባታዎችን በማከናወን ትልቅ ልምድ ያለው ኩባንያ ስለሆነ የነበሩ ልምዶቻችንን እያጎለበትን በጋራ አፍሪካን እንደምንገነባ እምነቴ ነው ብለዋል፡፡
ከጉብኝቱ በተጨማሪ የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴና ተልዕኮውን የሚያሳይ የ10 ደቂቃ ፕሮሞሽናል ዶክሜንታሪና የኮርፖሬሽኑን የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስርዓት ልዑካን በድኑ እንዲመለከቱ ተደርጓል፡፡
በዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት እና ካቢኔ ጽህፈት ቤት የፖሊሲ ትንተና፣ ማስተባበር እና የልማት እቅድ ምክትል ዋና ጸሃፊ ሚስተር ሚላርድ ማኑንጎ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ የተገጣጣሚ ህንፃ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ እየሰራቸው ባሉ ሥራዎች፣ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስርዓቱን ቀልጣፋና የመረጃ ልውዉጡን ፈጣን ለማድረግና የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ አምርቶ ለመጠቀም እያደረገው ያለውን ጥረት አድንቀው በቀጣይ በጋራ ከኮርፖሬሽኑ ጋር እንሰራለን ብለዋል፡፡