...

አቶ አመንቴ ዳዲ

የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ



የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት 
የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ተጠሪነቱ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡
1.    በዋና ሥራ አስፈጻሚው ለሚጠሩ ስብሰባዎች የሚቀርቡ አጀንዳዎችን አስፈላጊነት አይቶ ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ የስብሰባዎቹን ቃለ-ጉባዔዎች፣ ውሳኔዎችና ሰነዶች በሚገባ ተመዝግበው እንዲጠበቁ ያደርጋል፤ 
2.    ለጽ/ቤቱ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ክፍሎችን ያስተባብራል፤ ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ይመራል፤
3.    ጽ/ቤቱ እንዲያስተባብራቸው በኃላፊነት የተሰጡትን የሥራ ክፍሎች አፈፃፀም ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ለዋና ሥራ አስፈፃሚ ሪፖርት ያቀርባል፤
4.    የዋና ሥራ አስፈጻሚውን የዕለት ተዕለት መርሀ ግብሮችን ይከታተላል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤ 
5.    ከዋናሥራ አስፈጻሚው በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት የኮርፖሬሽኑን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ሲፀድቅም በአግባቡ መተግበሩን ያረጋግጣል፣
6.    ከኮርፖሬሽኑ የስትራቴጂያዊ ዕቅዱን መነሻ በማድረግ ለኮርፖሬሽኑ ተልዕኮ መሳካት የሚረዱ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን እንዲቀረፁ ደርጋል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤
7.    የኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ ፊሲካል ዕቅድ በአግባቡ መዘጋጀቱን ያረጋግጣል፤  ከፋይናንስ ዋና መምሪያ ለእያንዳንዱ ፊሲካል ዕቅድ በጀት መዘጋጀቱን ያረጋግጣል፤ 
8.    የኮርፖሬሽኑ ዘርፎችና የሥራ ክፍሎች ዓመታዊ ዕቅዳቸውን የኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት በማድረግ ማዘጋጀታቸውን በማረጋገጥ በስትራቴጂክ ማኔጅመንት እና በሥራ አመራር ቦርድ ያፀድቃል ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
9.    የኮርፖሬሽኑ የስትራቴጂያዊ እቅድ እና ዓመታዊ ዕቅድ በአግባቡ መዘጋጀቱን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤ የኮርፖሬሽኑ ዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማው የሥራ ክፍሎችንና የኮርፖሬሽኑን ተጨባጭ አፈጻጸም በሚያሳይና ለውሳኔ በሚያመች መልኩ እንዲፈጸም አስፈልጊውን ሁሉ ያደርጋል፤ ያረጋግጣል፤
10.    ከሌሎች በአገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር መሰል ተቋማት፤ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮችን ማከናወን እንዲቻል የውጭ ግንኙነት ሥራዎችን ፤ያስተባብራል፤
11.    የኮርፖሬሽኑን አሰራር ዘመናዊና በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያስጠናል፤ በጥናቱ መሠረት በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን መደገፍ የሚስፈልጋቸውን አሰራሮች እንዲለዩ ያደርጋል፤ የጥናት ውጤቱንም ለዋና ሥራ አስፈጻሚው ያቀርባል፤ ሲፈቀድም እንዲዘረጋ ያደርጋለ፤ አፈፃፀሙን ይቆጣጠራል፤
12.    የኮርፖሬሽኑን የኮሚኒኬሽንና የፕሮሞሽን ስርዓት እንዲቀረፅ ያደርጋል፤ የተቀረፀው ስርዓት በአግባቡ ተግባራዊ እተደረገ መሆኑን ይቆጣጠራል፤ ያረጋግጣል፤
13.    የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚከናወኑበትን መስፈርት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ የጥናት ስራዎች በመስፈርቱ መሠረት እየተሰሩ መሆኑንም ያረጋግጣል፤
14.    ኮርፖሬሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ ጥራታቸውን የጠበቁና ወጪ ቆጣቢ ማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ የምርትና የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በሚመለከት ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ተሞክሮዎችን እየተቀሰሙ እና ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር እየተቃኙ እንዲላመዱ የሚደረግበትን ስርአት ይቀርፃል፤ ጥቅም ላይ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤ 
15.    የጽ/ቤተን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በየወሩ፣ በሩብ ዓመት፣ በግማሽ ዓመት፣ በዘጠኝ ወርና በዓመት እንዲዘጋጅ በማድረግ ለዋና ሥራ አስፈጻሚው ያቀርባል፤
16.    ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ የሰው ሀብት እና ቋሚና አላቂ እቃዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፤ 
17.    ከሰው ኃበት ሥራ አመራር ዋና መምሪያ ጋር በመተባበር የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ሥልጠናና ትምህርት የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል፤
18.    በዋና ሥራ አስፈጻሚው የሚሰጡ ሌሎች ተዛማች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

Successfully subscribe !
Already subscribe with this email !