ከ4.1 ብር በላይ በሆነ ወጪ በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ ዙሪያ የሚገኘው የተንዳሆ ግድብና መስኖ ፕሮጀክት በ1997 ዓ.ም ተጀምሮ በ2009 ዓ.ም የተጠናቀቀው የተንዳሆ ግድብና የመስኖ ፕሮጀክት የ72 ኪሎ ሜትር የዋና ቦይ ግንባታ እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ እና የሶስተኛ ደረጃ ቦዮች. 1.8 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ያለው የተንዳሆ ግድብ 60,000 ሄክታር መሬት ማልማት ይችላል።
አዳዲስ ዜናዎች
የህንድ አምባሳደር የኮርፖሬሽኑን ኢንዱስትሪ ዞን ጎበኙ
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ራይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ዞን፣ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ማዕከልን፣ የኮንስትራክሽን ፕሮፌሽናል ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት እና የኢንፎርሜሽ ተጨማሪ ያንብቡ
ኮርፖሬሽኑ እና ዳን ሊፍት ቴክኖሎሎጂ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና ዳን ሊፍት ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ወገኖች በአሳንስር ምርት፣ ተከላ እና ጥገና የሥራ ትብብር ለማድረግ ያስችላቸዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እና የዳን ሊፍት ቴክኖሎጂ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል መብርሃቱ የመግባቢያ ስምምነቱን ፈርመዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ዕድሳትና ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እየተገነባ የሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት የህንጻ ዕድሳት እና ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡
በኮንትራት ስምምነቱ መሰረት የባለ ስድስት ወለል ህንጻ የዕድሳት ሥራ፣ የባለ ሁለት ወለል ካፍቴሪያ ግንባታ፣ የግቢ ማስዋብ ሥራ፣ የአስፋልት ንጣፍ እና የአጥር ሥራዎችን የሚያጠቃልለው ፕሮጀክት በተቀመጠለት የጥራት ደረጃ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አክሊሉ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥርዓቶችን በመጠቀም ግንባታውን በተቀላጠፈ መንገድ ለመምራት ከፍተኛ ጥረት ማደረጉን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ በቅርቡ ርክክብ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በጥሩ የግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ
የጊዳቦ ሎት 2 የቀኝ ቦይና መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለፕሮጀክቱ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሀብት አጠቃቀሙን በማሻሻሉና ሥራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራቱ ግንባታው በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታ 4,894 ሄክታር መሬትን በመስኖ በማልማት የአካባቢውን አርብቶ አደር ማህበረሰብ ወደ ከፊል አርብቶ አደርነት በመቀየር የንሮ ሁኔታውን ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡
ከ63 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ የመያዝ እና ከ13ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የማልማት አቅም ያለው የጊዳቦ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት ግንባታው ተጠናቆ ጥር 26 ቀን 2011ዓ.ም መመረቁ ይታወሳል፡፡
የልዑክ ቡድን አባላት የካም ሴራሚክንና ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን ኢንዱስትሪ ዞን ጎበኙ
በኢፌዲሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ
ፕሮጀክቱ በመልካም አፈጻፀም ላይ ይገኛል
በቢሾፍቱ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መልሶ ማስፈር እና ማቋቋም የባለ 7 ወለል ቅይጥ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት በመልካም አፈጻጸም ላይ ተጨማሪ ያንብቡ
Latest project
ዲማ - የራድ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
Transport sector / completed ____Date:Feb 9, 2023
ዲማ - 60 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የራድ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይገኛል። የውል ስምምነቱ በጥር 16 ቀን 2015 የተፈረመ ሲሆን የውል መጠኑ ብር 874,442,881 ነው። የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ ነው። ፕሮጀክቱ በዚህ አመት 2020 የተጠናቀቀ ሲሆን ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር ያገናኛል።