...

Corporation launches training institute, digital technology centre

ቀን: Nov 30, -1

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ቤቴል መንዲዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ የተከለሠ የኮንትራት ዋጋ እየተገነባ ያለውን ኮልፌ ቀራኒዮ አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክትን እስከ 2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለባለቤቱ ለማስረከብ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሆነ ተገለፀ፡፡

ግንባታው 2013 በጀት ዓመት መጨረሻ ሐምሌ ወር ላይ የተጀመረውን ይህን ፕሮጀክት እስከ 2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በሥራ ተቋራጩ፣ በባለቤቱ እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ሥራዎች በርብርብ እየተሠሩ እንደሆነ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር መረሳ ተስፋየ ገልፀዋል፡፡

ቀደም ሲል ከክፍያ ጋር በተያያዘ ለአራት ተከታታይ ወራት ግንባታው ቆሞ እንደነበር የገለፁት ኢንጂነር መረሳ ተስፋየ አሁን ላይ ችግሩ በመቀረፉ ሥራው በከፍተኛ ፍጥነትና ቁርጠኝነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡

ፕሮጀክቱን በታቀደው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለባለቤቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ለማስረከብ ፕሮጀክቱ በሁለት ሎት ተከፍሎ በሁለት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅና በሁለት ፈረቃ ማለትም 24 ሰዓት እየተሠራ እንደሆነ ነው ኢንጂነር መረሳ የገለፁት፡፡

ኢንጂነር መረሳ ተስፋየ ከዚህም ሌላ የሰው ኃይል በመጨመርና 17 ያህል ንዑስ ተቋራጮችንና የጉልበት ሥራ ተቋራጮችን በማስ

...

ፕሮጀክቱን ከተያዘለት ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው

ቀን: Nov 30, -1

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 15፣ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ፣ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ የተከለሠ የኮንትራት ዋጋ እየተገነባ ያለውን የአዲስ አበባ ከተማ መግቢያ እና መውጫ የግብርና ውጤቶች ማዕከልን ከተያዘለት ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሆነ ተገለፀ፡፡

እ.ኤ.አ. ታህሳስ 20 ቀን 2020 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2023 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ኮርፖሬሽኑ ከፕሮጀክቱ ባለቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር ውል መዋዋሉን የገለፁት የፕሮጀክቱ ሎት 1 ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዓለምአየሁ ካሣ ከተያዘለት የኮንትራት ጊዜ ቀድሞ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ኢንጂነር ዓለምአየሁ ፕሮጀክቱን ከተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ቀድሞ ለማጠናቀቅ በኮርፖሬሽኑ፣ በባለቤቱ እና በአማካሪ ድርጅቱ በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሆነ እና ለዚህም በየጊዜው የክትትል፣ ቁጥጥር እና ድጋፍ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ የፕሮጀክቱ የፊዚካል አፈፃፀም 70 በመቶ መድረሱን የተናገሩት ኢንጂነር ዓለምአየሁ ካሣ ፕሮጀክቱን ከኮንትራት ጊዜው አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ሥራው በሁለት ሎት ተከፍሎ በሁለት ሥራ አስኪያጆች እየተከናወነ፣ ከመደበኛ ሠራተኞችና የሥራ ሠዓት በተጨማሪ ንዑስ ሥራ ተቋራጮችን በማስገባት እና ተጨማሪ ሠዓት በመጠቀም እየተሠራ መሆኑን፤ የፕሮጀክቱ ባለቤትም ክፍያዎችን ሳያቆራርጥ እየፈፀመ እንዲሁም አማካሪ ድርጅቱ ከፍተኛ ክትትል እና ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሎት 2 ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አንዋር ንጉሤ በበኩላቸው በሎት 2 ሥር ያሉትን እንደ የአስተዳደር ህንፃ፣ የጅምላ መሸጫ ሱቆች፣ መጋዘኖ

...

ፕሮጀክቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል

ቀን: Nov 30, -1

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 2፣ ጀሞ ሚካኤል አካባቢ በ103.5 ሚሊዮን ብር የኮንትራት ዋጋ እየተገነባ ያለው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 G+4 አፓርትመንት ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ ባለ አራት ፎቅ ሁለት ብሎኮች (A&B) ያሉት ሲሆን አንደኛው ብሎክ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን እና የሁለተኛው ብሎክ አንዳንድ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ማለትም የበር እና የመስታወት ገጠማ፣ የኮሪደር ሴራሚክስ ማንጠፍና የቀለም ቅብ ሥራዎች በአንድ ሣምንት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ደስታ ገ/ህይወት ገልፀዋል፡፡  

በ868.32 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፉት ሁለቱ ብሎኮች እያንዳንዳቸው 32 መኖሪያ ቤቶችና 16 ሱቆች እንዳሏቸው ኢንጂነር ደስታ የገለፁ ሲሆን ፕሮጀክቱ እየተገነባ ያለው የአካባቢውን አቅመ ደካሞች ቤት ለማደስ በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

ግንባታው ታህሳስ 4 ቀን 2022 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት ከክፍያ ጋር በተያያዘ ሥራው ለሁለት ተከታታይ ወራት በመቆሙና በአገር አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የሲሚንቶ እጥረት ግንባታው ቢዘገይም ከኮንትራት ጊዜው ባጠረ ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ (ሥራው የቆመበትን ጊዜ ሳይጨምር) የአንድ ሳምንት ሥራ እንደቀረው ኢንጂነር ደስታ አክለው ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱን ግንባታ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እንደ ሥራ ተቋራጭ፣ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት የመከላከያ ሚኒስቴር እንደ ባለቤት እንዲሁም የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት እንደ አማካሪ ሆነው እያከናወኑት ይገኛል፡፡

...

የኮርፖሬሽኑ የአመራር አካላትና ሠራተኞች የሰንደቅ ዓላማ በዓልን አከበሩ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአመራር አካላትና ሠራተኞች የሉዓላዊነት ምልክት፣ የነፃነታችን አርማና የክብራችን መገለጫ

...

ፕሮጀክቱ የወሰን ማስከበር ችግር የሌለበትን የመንገድ አካል በዚህ ዓመት ያጠናቅቃል

ቀን: Nov 30, -1

የየካ ጣፎ ሎት 2 የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት የወሰን ማስከበር ችግር የሌለበትን የመንገድ አካል በተያዘው የበጀት ዓመት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገለጸ፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አብዮት ሲሳይ እንደተናገሩት በየካ ክፍለ ከተማ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የኮንትራት ዋጋ በኮርፖሬሽኑ እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ከወሰን ማስከበር ጋር በተገናኙ ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተጓጎለ ይገኛል፡፡

ኢንጂነር አብዮት ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም በፕሮጀክት ሳይቱ በመገኘት የመንገድ ሥራውን ለተመለከቱ የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች እንደተናገሩት 10.95 ኪ.ሜ ከሚረዝመው መንገድ ውስጥ 5.45 ኪ.ሜ የሚሆነው መንገድ ወይም የመንገዱ 50 በመቶ በወሰን ማስከበር ችግር ሊጀመር አልቻለም፡፡

ፕሮጀክቱ እስከ አሁን ድረስ በቅድሚያ ክፍያ መልክ ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ለተሰሩ ሥራዎች ክፍያ ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ የገለጹት ሥራ አስኪያጁ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የፊዚካል ሥራ አፈጻጸም 27 በመቶ እንደደረሰ ተናግረዋል፡፡

በፕሮጀክቱ የወርክ ኤክስኪዩሽን ቡድን መሪ ኢንጂነር ብሩክ ሽታዬ በበኩሉ የመንገድ ሥራው የ3.99 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ ሥራን፣ 6.69 የኮብልስቶን መንገድ ሥራን፣ የሁለት ድልድዮች ግንባታን፣ የአፈር መገደፊያ የኮንክሬት ግድግዳ ሥራዎችን እና የፍሳሽ ማስወገጃ ስትራክቸሮች ዝርጋታን እንደሚያካትት ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ፕሮጀክቱ 71 ቋሚ እና የኮንትራት ሠራተኞች ያሉት ሲሆን የወሰን ማስከበር ችግር የሌለበት የመንገዱ አካል ጠቅላላ ሥራ አፈጻጸም 78 በመቶ እንደደረሰ ጠቁመዋል፡፡    

...

Corporation strives to make CPDI centre of excellence

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የራሱን ተቋም ማለትም የግንባታ ባለሙያዎች ልማት ኢንስቲቲዩትን የብቃት ማዕከል ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገለጸ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር ግቢ በመገኘት ለ20 የግንባታ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠናን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ኢንስቲቲዩቱን የላቀ ዕውቀት ያለው የሰው ኃይል የሚፈራበት ተቋም የማድረግ ህልም እንዳለው ተናግረዋል፡፡

አብዛኞቹ ከሀገሪቱ የምህንድስና ትምህርት ቤቶች የሚመረቁ መሃንዲሶች መሰረታዊ የምህንድስና ዕውቀትና ክህሎት ይዘው እንደሚወጡ ይታወቃል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንስቲቲዩቱ በተለየ ሥልጠና ለሰልጣኞች ዘመኑን የዋጁ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችንና በልምድ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን የሚያስታጥቅ ተቋም ይሆናል ብለዋል፡፡

ተቋሙ ለኮርፖሬሽኑ የግንባታ አመራር አካላትና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ኢትዮጵያውያንና የውጭ ባለሙያዎች በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ሥራ አመራር ዘርፍ ገበያው የሚፈልገው የተማረ የሰው ኃይል ፍላጎት ልክ የተሰፉ ስልጠናዎችን የሚሰጥ ኢንስቲቲዩት እንዲሆን ይደረጋል ተብሏል፡፡  

በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ከአንድ ሺህ 500 በላይ የግንባታ መሃንዲሶች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አብዛኞቹ ባለሙያዎች በልምድ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን የሚያስተዋውቅ ስልጠና ማግኘት ይኖርባቸዋል በማለት አብራርተዋል፡፡  

እንደ ተቋሙ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አርጋው አሻ ገለጻ በተጠቀሰው ቀን በ20 የኮርፖሬሽኑ የግንበታ ፕሮጀክቶች ለተመደቡ ሥራ አስኪያጆች የሁለት ሳምንታት የድረ መረብ ስልጠና የተጀመረ ሲሆን በስልጠናዎች ማጠቃለያ ላይ ከምዘና በኋላ ከ40 የሚበልጡ መሃንዲሶች የፕሮጀክት ሥራ አመራር ሰርተፊኬት እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ ስልጠናዎች ኮርፖሬሽኑ ሜክ ኢንተርፕራይዝ እና ኮንስትራክሽን ሶሉሽንስ በሚባሉ የስልጠና ተቋማት ጋር በመተባበር እየተሰጡ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡