Organization Leaders, Prominent Engineers Provide Lectures to CPDI Trainees
ቀን: Dec 2, 2024
የዓለም ኢንጂነሮች ማህበራት ፌደሬሽን እና የአፍሪካ ኢንጂነሮች ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዚደንቶች እንዲሁም ታዋቂ መሃንዲሶች በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ በኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ልማት ተቋም ስልጠና እየተከታተሉ ለሚገኙ ሰልጣኞች በኮንስትራክሽን ምህንድስና ሙያ ላይ ያተኮረ ገለጻ አደረጉ፡፡
የዓለም ኢንጂነሮች ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ሙስጦፋ ባላራቤ ሸሁ፣ የአፍሪካ ኢንጂነሮች ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ካዛዋዲ ፓፒያስ ደደኪ፣ ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ፕሮፌሰር ፒ.ዲ. ርዋላሚላ እና ዮፍታሄ ዮሃንስ የተባሉ ባለሙያ ለሰልጣኝ ፊውቸር የፕሮጀክት ማኔጀሮች በምህንድስና ሙያ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል መሃንዲሶች ማህበር ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው የሁለት ቀናት የፊት ለፊት እና የድረ-መረብ (ዙም ቴክኖሎጂ) ስልጠና 35 የተቋሙ ሰልጣኞችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችን ያሳተፈ ነበር፡፡
Army commandants visit on-going project, corporation’s reform programs
ቀን: Dec 2, 2024
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌትናንት ጄነራል ሹማ አብደታ እንዲሁም የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል

ኮርፖሬሽኑ ቢግ 5 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን እየተሳተፈ ይገኛል
ቀን: Nov 28, 2024
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) በዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው ቢግ 5 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በኮንስትራክሽን ግብዓት ማኑፋክቸሪንግ ምርት እና በኮንስትራክሽን መስክ ያለውም አቅምና ምርት እያስተዋወቀ ሲሆን በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ገበያ ውስጥ በመግባት ተወዳዳሪነቱን ለማፋጠን እያከናወናቸው ያሉ ጥረቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ ኤግዚቢሽኑ ከህዳር 17-20ቀን 2017ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ነው፡፡

ኢሲሲ ጂ አይ ደብሊው ኃላ.የተ.የግ.ማህበር
ቀን: Nov 28, 2024
ኢትዮጵያ ኮንስራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) በ20.3 ቢሊዮን ብር ካፒታል በ2008 ዓ.ም የተቋቋመ የመንግስት ልማት ድርጅት ሲሆን ዋና ዋና
ቀን: Nov 28, 2024
ኢሲሲ-ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ከራይዚንግ ሆንግፋ ጋር በመሆን በሽርክና ካቋቋማቸው የምርት ማምረቻ ማዕከላት አንዱ ነው፡፡ የዚህን ማዕከል 70 በመቶ ድርሻ ኢ.ኮ.ሥ.ኮ ሲወስድ ቀሪውን 30 በመቶ ደግሞ የቻይና እና የህንድ ባለሀብቶች ይወስዳሉ፡፡ ማዕከሉ በሥሩ ሁለት የሥራ ክፍሎች ያሉት ሲሆን አንደኛው አገልግሎቱ ያለቀ ጎማን በመፍጨት ለእግረኛ እና ለመሮጫ ትራክ የሚያገለግሉ ምርቶችን ያመርታል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የተሻለ የጥራት ደረጃ ያላቸውን ሆሎ ኮር የህንፃ ወለል እና ግድግዳዎችን የሚያመርት ክፍል ነው፡፡ ሆሎ ኮር (ባለ ቀዳዳ) የህንፃ ወለል እና ግድግዳዎች ከተገጣጣሚ ህንጻ አካላት የሚመደቡ ሲሆን የህንፃው መሠረትና ስላብ የሚጠበቅባቸውን ጭነት እና ሌሎች ሁኔታዎችን የመቋቋም አቅማቸውን ሳያጡ የህንፃውን ጥቅል ክብደት የሚቀንሱ ኮንክሪትን በመጠቀም የሚመረቱ የህንፃ ወይም ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች ናቸው፡፡ በተገጣጣሚ ምርቶቹ ላይ ያሉት ባዶ ቦታዎች ወይም ክፍተቶች የህንፃውን መዋቅራዊ ጥንካሬ የማይቀነሱ ከመሆናቸው ሌላ ቀላል ክብደት ያላቸው በመሆናቸው ወደ ግንባታ ስፍራ እና በመገጣጠም ወቅት ለማንቀሳቀስ ምቹ ናቸው፤ እስከ 35 በመቶ የኮንክሪት ወጪን ለመቆጠብ ያስችላሉ፡፡ በእነዚህ ግብዓቶች የሚገነባ ህንፃ ጥሩ የድምፅ ስርገት የመቋቋም አቅም አለው፡፡ እሳትን ከመቋቋም እንፃርም ውጤታማ ግብዓቶች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ የቤቱን የሙቀትና ቀዝቃዜ መጠን የማመጣጠን ችሎታ አላቸው፡፡ ህንፃውን በቀላሉ በማፍረስ ምርቶቹን ለሌላ አገልግሎት ማዋል ይቻላል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥን የመቋቋም ችሎታቸውም ከፍተኛ ነው፡፡ ሆሎ ኮር የጥራት ደረጃውን የጠበቀ መደበኛ አርማታን እና በአንድ ላይ የተገመዱ ቴንሽን ገመዶችን በመጠቀም እና ቅድመ ቴንሽን የተደረጉ የሚመጣባቸውን ክብደት መቋቋም የሚችሉ ተገጣጣሚ ምርቶችን ያለምንም ሞልድ በማምረቻ ማሽኑ ቫይብሬሽን ብቻ የሚያመረት የማምረቻ ማሽን ነው፡፡ የማምረቻ ክፍሉ በመጀመሪያው የማስተዋወቂያ ጊዜ በመደበኛ የማምረት ሂደት በሳምንት 576ሜ2 ግድግዳ እና 1,200 የወለል ስፋት ስላብ ማምረት የሚችል ሲሆን የገብያ ፍላጎቱን መሰረት በማድረግ እስከ አራት እጥፍ ማምረት የሚያስችል እቅም አለው፡፡ ኢ.ኮ.ሥ.ኮ የ70 በመቶ ባለድርሻ እንደመሆኑ ግብዓቱን በሚሰራቸው ፕሮጀክቶቹ በመጠቀም አጠቃላይ ለህንፃው የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ እና ጥቅል የግንባታ እሴቶች ላይ አውንታዊ እምርታ በማምጣት ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
ኢሲሲ- ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ.የተ.የግ.ማህበር

የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት በሚል መሪ ቃል የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ተወያዩ
ቀን: Nov 28, 2024
የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች ከለውጡ ወዲህ ባለፋት ስድስት አመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ