...

የኢኮሥኮ ሴት ሠራተኞች የጠረጴዛ ቴኒስ ቡድን አቻውን 3 ለ 2 በሆነ ልዩነት አሸነፈ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) ባዘጋጀው የኢትዮጵያ ሠራተኞች የበጋ ወራት የ2ኛ ዲቪዚዮን የስፖርት ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) የሴት ሠራተኞች የጠረጴዛ ቴኒስ ቡድን አቻውን የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበርን 3 ለ 2 በሆነ ልዩነት ማሸነፉን የቡድኑ አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ታደሠ ገለጹ፡፡

ቅዳሜ፣ መጋቢት 07 ቀን 2016 ዓ.ም በመብራት ኃይል የቤት ውስጥ ስፖርት ማዘውተሪያ የተካሄደውን ይህንን ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር በማድረግ ተጋጣሚውን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ መቻሉን የገለፁት የቡድኑ አስተባባሪ ይህም ቡድኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መሻሻሎችን ማሳየቱን ያመለክታል ብለዋል፡፡

አስተባባሪው ለሥራ ውጤታማነትና የተሟላ ሰብዕናን ለመላበስ የኮርፖሬሽኑ ሴት ሠራተኞች በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

አቶ ዳንኤል የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞችም ቡድኖቹ በሚጫወቱባቸው ዕለታት ከመጫወቻ ሜዳዎች በመገኘት የኮርፖሬሽኑን ተጨዋቾች መደገፍ እና ማበረታት እንዳለባቸው ለኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

...

ሴት ሠራተኞች ለመብታቸው መከበር ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ተገለጸ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ሴት ሠራተኞች መብታቸውን በማስከበር ረገድ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የዓለም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው ውይይት ላይ በሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ የሥነ-ልቦና ሳይንስ ባለሙያ አቶ ኤልሻዳይ ተስፋ ጊዮርጊስ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ሃሰቦችን አቅርበዋል፡፡

የመምሪያው ተወካይ ወይዘሪት ኤልቤቴል መሃመድ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲቻል የሥራ ክፍሉ በመምሪያ ደረጃ የተዋቀረ ቢሆንም ሴት ሠራተኞች ዕድሉን በተሟላ መልኩ እየተጠቀሙበት እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡

“ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሠላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በውይይቱ ላይ በርካታ ሰብሳቢዎች ተገኝተዋል፡፡   

...

የወንዶች የጠረጴዛ ቴኒስ ቡድን አቻውን 3 ለ 0 አሸነፈ

ቀን: Nov 30, -1

በኢትዮጵያ ሠራተኞች የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) የወንድ ሠራተኞች የጠረጴዛ ቴኒስ ቡድን የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አቻውን በከፍተኛ የጨዋታ የበላይነት  3 ለ 0 በሆነ ልዩነት ማሸነፍ መቻሉን የቡድኑ አምበል አቶ ዳንኤል ታደሠ ገለፁ፡፡        

አቶ ዳንኤል የመጀመሪያው ዙር ውድድር መጠናቀቁንና የሁለተኛው ዙር ውድድር በቅርብ ጊዜ እንደሚጀምር የገለፁ ሲሆን ቡድናቸው ለዋንጫ ለሚደረገው ፉክክር ጠንክሮ እንደሚሠራ ገልፀዋል፡፡  

...

ኮርፖሬሽኑ ለሙስሊም ሠራተኞች የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቃሊቲ በሚገኘው የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ግቢ ለሙስሊም ሠራተኞች የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ፡፡ ኮርፖሬሽኑ የ1445ኛውን የረመዳን ጾም አስመልክቶ ባዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌውን ጨምሮ የስትራቴጂክ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በተዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ሙስሊም የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ኢትዮጵያዊ የሆነውን እና ላለፉት እልፍ ዓመታት የአገራችን ፅኑ መሰረት የሆነውን የአብሮነት፣ የፍቅር እና የወንድማማችነት ባህል ታሳቢ በማድረግ ፕሮግራሙን ላዘጋጁ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

...

ኮርፖሬሽኑ ለሙስሊም ሠራተኞች የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቃሊቲ በሚገኘው የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ግቢ ለሙስሊም ሠራተኞች የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ፡፡ ኮርፖሬሽኑ የ1445ኛውን የረመዳን ጾም አስመልክቶ ባዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌውን ጨምሮ የስትራቴጂክ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በተዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ሙስሊም የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ኢትዮጵያዊ የሆነውን እና ላለፉት እልፍ ዓመታት የአገራችን ፅኑ መሰረት የሆነውን የአብሮነት፣ የፍቅር እና የወንድማማችነት ባህል ታሳቢ በማድረግ ፕሮግራሙን ላዘጋጁ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

...

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የኢትዮጵያ የሥነ ጥበብ እና የሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ከንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከዋናው መስሪያ ቤት እና ከቃሊቲ የተውጣጡ 140 በላይ ሠራተኞች የኢትዮጵያ የሥነ ጥበብ