...

የኮርፖሬሽኑ የግማሽ አመት አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ

ቀን: Feb 27, 2025

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) 6 ወራት አፈፃፃም ገምግሟል።

 

ኮርፖሬሽኑ በእቅድ አፈጻጸሙ  የተሻለ አቋም ላይ እንደሚገኝ  የገለጸው ሆልዲንጉ  በተለይም በመሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም አመላክቷል፡፡

 

ኮርፖሬሽኑ ካለው አቅም አንጻር በቀጣይ የላቀ አፈጻጸም እንደሚያስመዘግብ ያለውን እምነት በመግለፅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

...

እንኳን ደስ አላችሁ!

ቀን: Feb 15, 2025

ላለፉት ሁለት ዓመታት በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ግንባታው የዘገየው በኢ.ኮ.ሥ.ኮ እየተገነባ የነበረው የያቤሎ ከተማ ባይፓስ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ የክልሉ መንግስት ችግሩን መፍታቱን ተከትሎ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

 

...

ኮርፖሬሽኑ በዓለም አቀፉ የመስኖ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ እየተሳተፈ ነው

ቀን: Feb 12, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን "የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ ጉባዔ እየተሳተፈ ነው፡፡

ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በጉባዔው የተለያዩ የዓለም ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡ ጎን ለጎንም የመስኖ ሥራዎችን የሚያሳይ አውደርዕይ ለእይታ ክፍት ተደርጓል።

በዚህ ጉባኤ እና አውደርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለመስኖ እና ለውሃ ሥራዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

...

ኮርፖሬሽኑ ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የፕሮጀክት ኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ

ቀን: Jan 29, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮሥኮ)  ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር  5.5 ቢሊዮን ብር በላይ የኮንትራት ዋጋ ያለው ፕሮጀክት  ለመገንባት የኮንትራት

...

ኮርፖሬሽኑ ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የፕሮጀክት ኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ

ቀን: Jan 29, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮሥኮ)  ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር  5.5 ቢሊዮን ብር በላይ የኮንትራት ዋጋ ያለው ፕሮጀክት  ለመገንባት የኮንትራት

...

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል

ቀን: Jan 27, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ባለፉት ዓመታት በሰው ኃብት ልማት፣ በዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎች ተከላ፣ አዳዲስ ሲስተሞችን በማበልጸግ እና የጥራት ፍተሻ ላቦራቶሪዎችን በማቋቋም የግንባታ ጥራትን እና ተወዳዳሪነቱን ከማሳደጉም ባሻገር ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር ሽርክና በመመስረት የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በማምረት የራሱን የግብዓት ፍላጎት ከማሟላት አልፎ ለገበያ በማቅረብ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን እየተካ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ይችል ዘንድ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ልህቀት ማዕከልን ያቋቋመ ሲሆን በማዕከሉ ስር ደግሞ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን አንድ ቦታ ሆኖ ለመቆጣጠር የሚያስችል የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል አደራጅቷል፡፡

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል ዋና ዓላማ 16ቱን የፕሮጀክት ማናጅመንት የዕውቀት መስኮች ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት የፕሮጀክቶችን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እና የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥርዓቱን ዘመናዊ ማድረግ ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል በተለያዩ የሥራ ቡድኖች የተዋቀረ እና በራስ ዓቅም የለሙ የተለያዩ ሶፍትዌሮች ያሉት ሲሆን ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ዕለታዊ የሥራ አፈጻጸም መከታተያ ሲስተም  የተሽከርካሪዎች ማኔጅመንት ሲስተም  እና የተቀናጀ የሀብት አስተዳደር አመራር ስርዓት (ERP) ይገኙበታል፡፡

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል የተቋሙን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ሁለንተናዊ የሥራ እንቅስቃሴ በአንድ ቦታ ላይ ሆኖ ለመቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ኮርፖሬሽኑ ያለውን የሰው ኃብት እና ሌሎች ሀብቶችን ከወረቀት ነጻ በሆነ የሥራ አመራር ሥርዓት እንዲመራ የሚያስችል ነው፡፡