የኮርፖሬሽኑ ዳራ


የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 366/2008 ታህሳስ 08 ቀን የቀድሞ የኢትዮጵያ መንገድ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅትን በማዋሀድ ከዚያም በተሻሻለው በሚንስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 390/2008 የቀድሞው የኢትዮጵያ ተገጣጣሚ ህንፃ አካላት ማምረቻ ድርጅትን ወደ ኮርፖሬሽኑ በመቀላቀል በ20,313,608,143.90 ብር የተፈቀደ ካፒታል የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ከማቋቋሚያ ካፒታሉ መካከልም 15,598,806,251.43 ብር በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ተከፍሎታል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ነው፡፡ ፖሊሲ አውጪው አካል ደግሞ የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ ሲሆን በመንግስት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሰረት ይተዳደራል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በአምስት ዘርፎች ፣ በሰባት ማዕከላትና በሁለት ቅርንጫፎች የተደራጀ ነው፡፡ እነርሱም የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ የውሃ መሰረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ የህንጻና ቤቶች ኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ የኮርፖሬት ኃብት አስተዳደርና ሠርቪስ ዘርፍ እና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ሲሆኑ ማዕከላቱ ደግሞ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችና ማሽነሪዎች አስተዳደር ማዕከል፣ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች መገጣጠሚያና ጥገና ማዕከል፣ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል፣  የግብዓት ማምረቻ ማዕከል፣ የመስኖና ግብርና ልማት ማዕከል፣ የቤቶች ልማት ማዕከል እና የሪል እስቴት ልማት ማዕከል ናቸው፡፡ በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ  በጂቡቲ የጂቡቲ ቅርንጫፍ  እና  በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን የሚያስተባብር ማዕከላዊ ቅርንጫፍ አለው፡፡ 
የኮርፖሬሽኑ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ከተማ ሆኖ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ የመንገድ፣ የድልድይ፣ የኤርፖርት፣ የመጠጥ ውሃ፣ የመስኖ ውሃ ግድብ ግንባታ እና ጥገና ፕሮጀክቶች አሉት፡፡ እንዲሁም በአንድ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ በአምስት የዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና በየደረጃው በሚገኙ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ይመራል

 

 

 

Successfully subscribe !
Already subscribe with this email !