...

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል

ቀን: Jan 27, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ባለፉት ዓመታት በሰው ኃብት ልማት፣ በዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎች ተከላ፣ አዳዲስ ሲስተሞችን በማበልጸግ እና የጥራት ፍተሻ ላቦራቶሪዎችን በማቋቋም የግንባታ ጥራትን እና ተወዳዳሪነቱን ከማሳደጉም ባሻገር ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር ሽርክና በመመስረት የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በማምረት የራሱን የግብዓት ፍላጎት ከማሟላት አልፎ ለገበያ በማቅረብ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን እየተካ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ይችል ዘንድ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ልህቀት ማዕከልን ያቋቋመ ሲሆን በማዕከሉ ስር ደግሞ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን አንድ ቦታ ሆኖ ለመቆጣጠር የሚያስችል የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል አደራጅቷል፡፡

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል ዋና ዓላማ 16ቱን የፕሮጀክት ማናጅመንት የዕውቀት መስኮች ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት የፕሮጀክቶችን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እና የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥርዓቱን ዘመናዊ ማድረግ ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል በተለያዩ የሥራ ቡድኖች የተዋቀረ እና በራስ ዓቅም የለሙ የተለያዩ ሶፍትዌሮች ያሉት ሲሆን ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ዕለታዊ የሥራ አፈጻጸም መከታተያ ሲስተም  የተሽከርካሪዎች ማኔጅመንት ሲስተም  እና የተቀናጀ የሀብት አስተዳደር አመራር ስርዓት (ERP) ይገኙበታል፡፡

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል የተቋሙን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ሁለንተናዊ የሥራ እንቅስቃሴ በአንድ ቦታ ላይ ሆኖ ለመቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ኮርፖሬሽኑ ያለውን የሰው ኃብት እና ሌሎች ሀብቶችን ከወረቀት ነጻ በሆነ የሥራ አመራር ሥርዓት እንዲመራ የሚያስችል ነው፡፡ 

...

የከባድ ተሽከርካሪዎች ጥገና

ቀን: Jan 10, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ለተከታታይ ዓመታት ባካሄዳቸው የለውጥ ሥራዎች አማካኝነት ከተመዘገቡ ከፍተኛ ውጤቶች መካከል አንዱ በተቋሙ የኢንዱስትሪ ማናጅመንት ዘርፍ፣ በአውቶሞቲቭ እና ማሽነሪ ጥገና ማዕከል ሥር የተቋቋመው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጥገና መምሪያ ነው፡፡

የከባድ ተሸከርካሪ ጥገና መምሪያ በሦስት ቡድኖች የተዋቀረ ሲሆን እነሱም ከባድ ተሸከርካሪዎች ጥገና፣ ሞተር ጥገና እና የተሸከርካሪዎች የአካል መገጣጠምና ቀለም ቅብ ቡድኖች ናቸው፡፡ መምሪያው በቀን ለ24 ሰዓታት በሁለት ሽፍት የሚሰጣቸው የጥገና አይነቶች ሁለት ሲሆኑ እነሱም የተሽከርካሪ አካል እድሳት እና የተሽከርካሪ አካልና የመለወጥ ሥራዎች ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት የተሽከርካሪዎች ቀለም ቅብ ሥራ የሚከናወነው “ካር ቡዝ” በተሰኘ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ቀለም መቀቢያ ቴክኖሎጂ ሲሆን እስከ አሁን በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የጥገና ማዕከላት ውስጥ ብቸኛው የቴክኖሎጂ ተጠቀሚ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ነው፡፡  

የተሽከርካሪ አካል መለወጥ ሥራን በተመለከተ መምሪያው አገልግሎት የማይሰጥን አውቶቡስ የአካል ለውጥ በማድረግ “ሳፋሪ ባስ” የተሰኘች ለቱሪስቶች አመቺ የሆነች ተሽከርካሪ ሰርቶ ለአገልግሎት ብቁ ያደረገ ሲሆን ልምዱን ለሌሎች መሰል ተቋማት ለማካፈል ዝግጁ እንደሆነ መምሪያው ገልጿል፡፡

መምሪያው ለውስጥ እና ለውጭ ደንበኞች የከባድ ተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አሁን ላይ የውጭ ደንበኞቹ ቁጥር 22 ደርሷል፡፡ ጥቂቶቹን ለመግለጽ ያህል መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የመንግስት የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይገኙበታል፡፡

...

Light vehicle maintenance workshop

ቀን: Jan 1, 2025

ይህ ዎርክ ሾፕ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ የተደራጀ ሲሆን በቀን 35 መኪናዎችን የመጠገን አቅም አለው፡፡ የዚህ ወርክሾፕ መቋቋም ዋና ዓላማ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ዘርፈ

...

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ቀን: Dec 26, 2024

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግንባታ ግብዓት አቅርቦት እና በሌሎች መስኮች

...

አገልግሎት የሰጠ ጎማን መልሶ መጠቀም የሚያችል ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

ቀን: Dec 24, 2024

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) እና ራይዚንግ ሆንግፋ ኩባንያ መካከል በሽርክና የተቋቋመው ጎማን መልሶ መጠቀም የሚያስችል ፋብሪካ ከታህሳስ 09 ቀን 2017 ጀምሮ የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ፡፡

የፋብሪካና ምርት ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ቅዱስ ወ/ማርያም ለኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባልደረቦች እንደተናገሩት ፋብሪካው ጥቅም ከሰጡ ጎማዎች ሽቦዎችን አውጥቶ፣ ጎማውን ቆራርጦ እና ፈጭቶ በቀን እስከ 600 ኪሎ ግራም የጎማ ዱቄት ማምረት ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ የጎማ ጡቦችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ የመሮጫ መሞችን እና የህጻናት መጫወቻ ቦታዎችን መስራት እንደሚያስችል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የቃሊቲ ኢንዱስትሪ ዞን የተተከለው ፋብሪካ እስከ አሁን ድረስ ከ30 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደፈጠረ ከኢንጂነሩ ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡

...

Deputy PM Visits Corporation’s Industry Zone

ቀን: Dec 14, 2024

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ( ...) ካነገበው ራእይ እና ተልእኮ አንጻር  በአፍሪካ ምርጥ ሦስት የኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያዎች መካከል