...

ኮርፖሬሽኑ የራሱን ተቋም የብቃት ማዕከል ለማድረግ እየጣረ ነው

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የራሱን ተቋም ማለትም የግንባታ ባለሙያዎች ልማት ኢንስቲቲዩትን የብቃት ማዕከል ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገለጸ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር ግቢ በመገኘት ለ20 የግንባታ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠናን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ኢንስቲቲዩቱን የላቀ ዕውቀት ያለው የሰው ኃይል የሚፈራበት ተቋም የማድረግ ህልም እንዳለው ተናግረዋል፡፡

አብዛኞቹ ከሀገሪቱ የምህንድስና ትምህርት ቤቶች የሚመረቁ መሃንዲሶች መሰረታዊ የምህንድስና ዕውቀትና ክህሎት ይዘው እንደሚወጡ ይታወቃል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንስቲቲዩቱ በተለየ ሥልጠና ለሰልጣኞች ዘመኑን የዋጁ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችንና በልምድ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን የሚያስታጥቅ ተቋም ይሆናል ብለዋል፡፡

ተቋሙ ለኮርፖሬሽኑ የግንባታ አመራር አካላትና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ኢትዮጵያውያንና የውጭ ባለሙያዎች በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ሥራ አመራር ዘርፍ ገበያው የሚፈልገው የተማረ የሰው ኃይል ፍላጎት ልክ የተሰፉ ስልጠናዎችን የሚሰጥ ኢንስቲቲዩት እንዲሆን ይደረጋል ተብሏል፡፡  

በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ከአንድ ሺህ 500 በላይ የግንባታ መሃንዲሶች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አብዛኞቹ ባለሙያዎች በልምድ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን የሚያስተዋውቅ ስልጠና ማግኘት ይኖርባቸዋል በማለት አብራርተዋል፡፡  

እንደ ተቋሙ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አርጋው አሻ ገለጻ በተጠቀሰው ቀን በ20 የኮርፖሬሽኑ የግንበታ ፕሮጀክቶች ለተመደቡ ሥራ አስኪያጆች የሁለት ሳምንታት የድረ መረብ ስልጠና የተጀመረ ሲሆን በስልጠናዎች ማጠቃለያ ላይ ከምዘና በኋላ ከ40 የሚበልጡ መሃንዲሶች የፕሮጀክት ሥራ አመራር ሰርተፊኬት እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ ስልጠናዎች ኮርፖሬሽኑ ሜክ ኢንተርፕራይዝ እና ኮንስትራክሽን ሶሉሽንስ በሚባሉ የስልጠና ተቋማት ጋር በመተባበር እየተሰጡ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡    

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኮርፖሬሽኑን ለሰልጣኞች አስተዋወቁ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ልማት ተቋም ውስጥ ለሚሰለጥኑ የነገ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች ገለጻ አደረጉ፡፡

በኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት የሰው ኃብት አስተዳደርና ሰርቪስ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዋቅጂራ ይልማ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የማስተዋወቂያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ለሰልጣኞች እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ በጣም ግዙፍ የመንግስት የልማት ተቋም እንደመሆኑ አሁን ላይ ዘርፈ-ብዙ የግንባታ ሥራዎችን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ የተመዘገበ ካፒታል ያለው ይህ የግንበታ ተቋም በትራንስፖርት እና የውሃ መሰረተ ልማት ግንባታ፣ በህንጻና ቤቶች ልማት፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረት፣ በግብርና ልማት፣ በሪል ስቴት ልማት ሥራዎች እና በሌሎች በርካታ የግንባታ ሥራዎች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አብራርተዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በርካታ የተማረ የሰው ኃይል እና ከ2 ሺህ በላይ የግንባታ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ያሉት ድርጅት ነው ያሉት አቶ ዋቅጂራ ወደፊት ኮርፖሬሽኑ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለመላ ሀገሪቱ የሚበቁ የላቀ ሙያ ያላቸው የግንባታ ባለሙያዎችን ለማፍራት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ልማት ተቋም ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አርጋው አሻ በበኩላቸው ተቋሙ ሰልጣኞችን በፕሮጀክት ሥራ አመራር የበቁ ባለሙያዎች እንዲሆኑ ለማስቻል 16 የዕውቀት መስኮችን መሰረት ባደረገ መልኩ የቲዮሪ እና የተግባር ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቅቋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር አርጋው እንደተናገሩት በሃገር ደረጃ የሚታዩ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታ ሥራዎች፣ በወጪ እና በሰዓት አጠቃቀም በኩል ያሉ ብክነቶች፣ እንዲሁም በግንባታው ዘርፉ እየተስፋፉ የሚገኙ ብልሹ አሰራሮች ኮርፖሬሽኑ እንደ መንግስት የልማት ተቋም የፕሮጀክት ሥራ አመራር ስልጠናን እንዲጀምር አስገድደውታል ብለዋል፡፡

ሰልጣኞች ለስድስት ወራት የሚሰጠውን የቲዮሪ እና የተግባር ስልጠና አጠናቅቀው የምዘና ፈተናውን ካለፉ በኋላ የሁለት ዓመት አገልግሎት እንዳለው ጀማሪ የፕሮጀክት ሥራ አስኪጅ መብትና ጥቅማ ጥቅም ይኖራቸዋል በማለት ዶ/ር አርጋው አስረድተዋል፡፡

...

Corporation launches training institute, digital technology centre

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ማበልጸጊያ ኢንስቲትዩትንና  የግንባታ ሥራዎችን በማዕከል ሆኖ መከታተል የሚያስችል የዲጂታል ቴክኖሎጂ ማዕከልን ሥራ አስጀመረ፡፡

አዲሱ የስልጠና ተቋም ወደፊት በዕውቅት የዳበሩ የግንባታ ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችል ሲሆን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ማዕከሉ ደግሞ በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጅቶችን በአንድ ማዕከል መከታተል የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ተገንብተው ወደ ሥራ የገቡት ሁለቱ ተቋማት ኮርፖሬሽኑ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በላቀ ጥራት፣ በተያዘላቸው ጊዜ እና በተመደበላቸው የወጪ መጠን አጠናቅቆ ለማስረከብ የሚያስችሉት መሆኑን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ተናግረዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስትር

...

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለሰልጣኝ ፕሮጀክት ማናጀሮች መልዕክት አስተላለፉ

ቀን: Nov 30, -1

ኃላፊነት በአግባቡ የመወጣት አቅምና ዲሲፕሊን ከፕሮጀክት ማናጀሮች እንደሚጠበቅ ፕሮጀክት ማናጀሮችን ለማፍራት በተዘጋጀ የስልጠና ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተናገሩ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ የገበያ አድማሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማስ

...

የድርጅት አቀፍ ሲስተም አተገባበር ውጤታማ ለማድረግ ለሥራ አስኪያጆች ስልጠና ተሰጠ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተገባራዊ እያደረገ የሚገኘውን የድርጅት አቀፍ ሲስተም (Enterprise Resource Planning) ውጤታማ ለማድረግና ተቋማዊ ለውጡን ለማፋጠን በአዲስ አበባ ዙሪያ ለሚገኙ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች ስልጠና መሰጠቱን የኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡