...

የህንድ አምባሳደር የኮርፖሬሽኑን ኢንዱስትሪ ዞን ጎበኙ

ቀን: Apr 15, 2025

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ራይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ዞን፣ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ማዕከልን፣ የኮንስትራክሽን ፕሮፌሽናል ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት እና የኢንፎርሜሽ

...

ኮርፖሬሽኑ እና ዳን ሊፍት ቴክኖሎሎጂ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ቀን: Apr 3, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና ዳን ሊፍት ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር  በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ወገኖች በአሳንስር ምርት፣  ተከላ እና ጥገና  የሥራ ትብብር ለማድረግ ያስችላቸዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እና የዳን ሊፍት ቴክኖሎጂ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል መብርሃቱ  የመግባቢያ ስምምነቱን ፈርመዋል።

...

የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ዕድሳትና ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

ቀን: Mar 27, 2025

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እየተገነባ የሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት የህንጻ ዕድሳት እና ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡

በኮንትራት ስምምነቱ መሰረት የባለ ስድስት ወለል ህንጻ የዕድሳት ሥራ፣ የባለ ሁለት ወለል ካፍቴሪያ ግንባታ፣ የግቢ ማስዋብ ሥራ፣ የአስፋልት ንጣፍ እና የአጥር ሥራዎችን የሚያጠቃልለው ፕሮጀክት በተቀመጠለት የጥራት ደረጃ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አክሊሉ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥርዓቶችን በመጠቀም ግንባታውን በተቀላጠፈ መንገድ ለመምራት ከፍተኛ ጥረት ማደረጉን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ በቅርቡ ርክክብ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡

...

ፕሮጀክቱ በጥሩ የግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

ቀን: Mar 21, 2025

የጊዳቦ ሎት 2 የቀኝ ቦይና መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተገልል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለፕሮጀክቱ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሀብት አጠቃቀሙን በማሻሻሉና ሥራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራቱ ግንባታው በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ 4,894 ሄክታር መሬትን በመስኖ በማልማት የአካባቢውን አርብቶ አደር ማህበረሰብ ወደ ከፊል አርብቶ አደርነት በመቀየር የንሮ ሁኔታውን ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡ 

ከ63 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ የመያዝ እና ከ13ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የማልማት አቅም ያለው የጊዳቦ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት ግንባታው ተጠናቆ ጥር 26 ቀን 2011ዓ.ም መመረቁ ይታወሳል፡፡

...

የልዑክ ቡድን አባላት የካም ሴራሚክንና ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን ኢንዱስትሪ ዞን ጎበኙ

ቀን: Mar 17, 2025

በኢፌዲሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት / ጫልቱ ሳኒ እና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

...

ፕሮጀክቱ በመልካም አፈጻፀም ላይ ይገኛል

ቀን: Mar 15, 2025

በቢሾፍቱ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የኢትዮጵያ  አየር መንገድ ግሩፕ መልሶ ማስፈር  እና  ማቋቋም የባለ 7 ወለል ቅይጥ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት በመልካም አፈጻጸም ላይ