...

አገልግሎት የሰጠ ጎማን መልሶ መጠቀም የሚያችል ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

ቀን: Dec 24, 2024

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) እና ራይዚንግ ሆንግፋ ኩባንያ መካከል በሽርክና የተቋቋመው ጎማን መልሶ መጠቀም የሚያስችል ፋብሪካ ከታህሳስ 09 ቀን 2017 ጀምሮ የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ፡፡

የፋብሪካና ምርት ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ቅዱስ ወ/ማርያም ለኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባልደረቦች እንደተናገሩት ፋብሪካው ጥቅም ከሰጡ ጎማዎች ሽቦዎችን አውጥቶ፣ ጎማውን ቆራርጦ እና ፈጭቶ በቀን እስከ 600 ኪሎ ግራም የጎማ ዱቄት ማምረት ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ የጎማ ጡቦችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ የመሮጫ መሞችን እና የህጻናት መጫወቻ ቦታዎችን መስራት እንደሚያስችል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የቃሊቲ ኢንዱስትሪ ዞን የተተከለው ፋብሪካ እስከ አሁን ድረስ ከ30 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደፈጠረ ከኢንጂነሩ ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡

...

Deputy PM Visits Corporation’s Industry Zone

ቀን: Dec 14, 2024

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ( ...) ካነገበው ራእይ እና ተልእኮ አንጻር  በአፍሪካ ምርጥ ሦስት የኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያዎች መካከል

...

Flexi Flume Factory

ቀን: Dec 5, 2024

 

የፍሌክሲ ፍሉም ፋብሪካ በቀድሞው የኢትዮጵያ ውሃ ሥራዎች ድርጅት በ1999 ዓ.ም የተቋቋመ ፋብሪካ ሲሆን የስኳር ፋብሪካዎችን የፍሌክሲ ፍሉም ፍላጎት ለማሟላት ታልሞ የተመሰረተ ኩባንያ ነበር፡፡ በሒደት በተፈጠሩ የተለያዩ ምክንያቶች ፋብሪካው ትኩረት ተነፍጎት ማምረት ያቆመባቸው ጊዚያት ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሦስት የተለያዩ የመንግስት ተቋማት በማዋሃድ በ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን መመስረትና በ2012 ዓ.ም ኮርፖሬሽኑ ባከናውነው የሪፎርም ሥራዎች ህይወት ከዘራባቸው ጉዳዮች አንዱ የፍሌክሲ ፍሉም ፋብሪካ እንደ አዲስ ወደ ሥራ መግባትና ወደ ምርት መሸጋገር ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከተመሰረተ በኋላ የገበያ ፍላጎቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የፍሌክሲ ፍሉም ፋብሪካን እንደ አዲስ እንዲከፈት ከማድረጉም በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት የተለያየ መጠን ያላቸው የአፈርና የእህል መያዣ/ከረጢቶች፣ ለተለያዩ የኮንስትራክሽን ሳይቶች ከለላ የሚሆኑ ሸራዎችንና  ለመስኖ አገልግሎት  የሚሆኑ ፓይፖችን አምርቶ ከመጠቀም ባለፈ ከውጪ የሚገቡ የአፈርና የእህል ማዳበሪያ ከረጢቶችን  በሀገር ውስጥ አምርቶ ለገበያ በማቅረብ  የውጪ ምንዛሬን እያዳነ ይገኛል፡፡   

በተለይ የአፈር ማዳበሪያን  ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ አስገብቶ ለማከፋፈል የሚያገለግሉ የአፈር ማዳበሪያ ከረጢቶችን አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ በትኩረት እየሰራ ሲሆን የሙከራ ምርቶችን የማምረት ሥራ አከናውኗል፡፡ ምርቶችን በሚፈለገው መጠን ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ በፈረቃ የማምረት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የፍሌክሲ ፍሉም ፋብሪካው ስድስት ማሽኖች ያሉት ሲሆን በቀን በእያንዳንዱ ማሽን ሦስት ሺህ በድምሩ 18 ሺህ ከረጢት ማዳበሪያዎች እና 18 ሺህ ብትን ከረጢት(ሺት) ያመርታል፡፡ በተጨማሪም  በሰዓት 255 ሸራ (ላምኔትድ ፒፒ)  በኬጅ እና በሰዓት ሦስት ሺህ ፍሌክሲ ፍሉም ፓይፕ በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

 

...

Organization Leaders, Prominent Engineers Provide Lectures to CPDI Trainees

ቀን: Dec 2, 2024

የዓለም ኢንጂነሮች ማህበራት ፌደሬሽን እና የአፍሪካ ኢንጂነሮች ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዚደንቶች እንዲሁም ታዋቂ መሃንዲሶች በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ በኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ልማት ተቋም ስልጠና እየተከታተሉ ለሚገኙ ሰልጣኞች በኮንስትራክሽን ምህንድስና ሙያ ላይ ያተኮረ ገለጻ አደረጉ፡፡

የዓለም ኢንጂነሮች ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ሙስጦፋ ባላራቤ ሸሁ፣ የአፍሪካ ኢንጂነሮች ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ካዛዋዲ ፓፒያስ ደደኪ፣ ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ፕሮፌሰር ፒ.ዲ. ርዋላሚላ እና ዮፍታሄ ዮሃንስ የተባሉ ባለሙያ ለሰልጣኝ ፊውቸር የፕሮጀክት ማኔጀሮች በምህንድስና ሙያ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል መሃንዲሶች ማህበር ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው የሁለት ቀናት የፊት ለፊት እና የድረ-መረብ (ዙም ቴክኖሎጂ) ስልጠና 35 የተቋሙ ሰልጣኞችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችን ያሳተፈ ነበር፡፡

...

Army commandants visit on-going project, corporation’s reform programs

ቀን: Dec 2, 2024

የኢ... መከላከያ ሠራዊት የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌትናንት ጄነራል ሹማ አብደታ እንዲሁም የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል

...

ኮርፖሬሽኑ ቢግ 5 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን እየተሳተፈ ይገኛል

ቀን: Nov 28, 2024

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) በዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው ቢግ 5 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በኮንስትራክሽን ግብዓት ማኑፋክቸሪንግ ምርት እና በኮንስትራክሽን መስክ ያለውም አቅምና ምርት እያስተዋወቀ ሲሆን በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ገበያ ውስጥ በመግባት ተወዳዳሪነቱን ለማፋጠን እያከናወናቸው ያሉ ጥረቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ ኤግዚቢሽኑ ከህዳር 17-20ቀን 2017ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ነው፡፡