...

የብረት መቁረጫና ማጠፊያ ዎርክሾፕ

ቀን: Mar 4, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የብረት መቁረጫና ማጠፊያ (Rebar cutting and bending) ዎርክሾፕ በማደራጀት አስፈላጊ የብረት ግብዓቶችን በማዕከል ደረጃ ለፕሮጀክቶች እያቀረበ ይገኛል፡፡

ይህ ዎርክሾፕ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ክፍሎችና ፕሮጀክቶች በሚያቀርቡት መጠንና ስኬጁል መሰረት ብረትን በመቁረጥ፣ በማጠፍና በሚፈለገው መንገድ በማስተካከል ብረቱ ጥቅም ላይ ወደ ሚውልበት ፕሮጀክት አንዲደርስ እያደረገ ይገኛል፡፡፡

ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ የተቆረጡና የታጠፉ ብረቶች  ከአንድ ማዕከል እንዲቀርቡ መደረጉ የብረት አጠቃቀም እንዲሻሻል፣  ብክነት እንዲቀንስ፣  ፕሮጀክቶች ብረት በመቁረጥና በማጠፍ

...

ፕሮጀክቱ በማጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ ይገኛል

ቀን: Feb 28, 2025

ዘርፈ-ብዙ አገልግሎቶችን የሚሰጡ የበርካታ ህንፃዎችን፣ መጋዘኖችን፣ ሼዶችን፣ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን፣ የአጥርና ሌሎች የግንባታ ሥራዎችን ያካተተው ኃይሌ ጋርመንት የግብርና ውጤቶች ገበያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ መገኘቱ ተገለጸ፡፡
ግንባታቸው በመከናወን ላይ ከሚገኘው የማዕከሉ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ውጭ ሌሎች ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የተገለጸ ሲሆን የተጠቀሱት ቀሪ ሥራዎች በቀርብ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ፡፡

...

የኮርፖሬሽኑ የግማሽ አመት አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ

ቀን: Feb 27, 2025

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) 6 ወራት አፈፃፃም ገምግሟል።

 

ኮርፖሬሽኑ በእቅድ አፈጻጸሙ  የተሻለ አቋም ላይ እንደሚገኝ  የገለጸው ሆልዲንጉ  በተለይም በመሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም አመላክቷል፡፡

 

ኮርፖሬሽኑ ካለው አቅም አንጻር በቀጣይ የላቀ አፈጻጸም እንደሚያስመዘግብ ያለውን እምነት በመግለፅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

...

እንኳን ደስ አላችሁ!

ቀን: Feb 15, 2025

ላለፉት ሁለት ዓመታት በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ግንባታው የዘገየው በኢ.ኮ.ሥ.ኮ እየተገነባ የነበረው የያቤሎ ከተማ ባይፓስ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ የክልሉ መንግስት ችግሩን መፍታቱን ተከትሎ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

 

...

ኮርፖሬሽኑ በዓለም አቀፉ የመስኖ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ እየተሳተፈ ነው

ቀን: Feb 12, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን "የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ ጉባዔ እየተሳተፈ ነው፡፡

ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በጉባዔው የተለያዩ የዓለም ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡ ጎን ለጎንም የመስኖ ሥራዎችን የሚያሳይ አውደርዕይ ለእይታ ክፍት ተደርጓል።

በዚህ ጉባኤ እና አውደርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለመስኖ እና ለውሃ ሥራዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

...

ኮርፖሬሽኑ ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የፕሮጀክት ኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ

ቀን: Jan 29, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮሥኮ)  ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር  5.5 ቢሊዮን ብር በላይ የኮንትራት ዋጋ ያለው ፕሮጀክት  ለመገንባት የኮንትራት