...

የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች በሞጆ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (...) የሥራ መሪዎች እና ሠራተኞች በሞጆ ከተማ

...

ከኮርፖሬሽኑ ጋር በሽርክና እየሰራ የሚገኘው የካም ሴራሚስ ፋብሪካ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ወደ ምርት እንደሚገባ ተገለፀ

ቀን: Nov 30, -1

የካም ሴራሚስ ፋብሪካ  ዋና ሥራ አስኪያጅ  አቶ ዋሪዮ በርገሮ እንደተናገሩት  ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በሽርክና መሥራት መቻላችን ተጨማሪ   አቅም  የፈጠረ ሲሆን  ፋብሪካውን ሥራ ለማስጀመር የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እስከ መስከረም መጨረሻ አጠናቀን  በ2017ዓ.ም ጥቅምት ወር  መጀመሪያ ወደ ምርት ለመግባት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡ ፋብሪካው  በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ 18400 ስኩየር ሜትር የተለያዩ የግድግዳ እና የወለል ሴራሚክ ውጤቶችን በቀን የማምረት አቅም ያለው ሲሆን ከውጪ የሚገባውን ሴራሚክ ለመቀነስ እና እንደ ሀገር የሚስተዋለውን  ከፍተኛ  የሆነ የሴራሚክ ፍላጎት  በተቻለ አቅም ለማቅረብ የራሱ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ፋሪካው በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ ሲገባ ለ1200 ዜጎችም የሥራ አድል እንደሚፈጥር ሥራ አስኪያጁ አያይዘው ገልፀዋል፡፡

የካም ሴራሚክስ ፋብሪካ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በቅርቡ በሽርክና ለመስራት የሚያስችላቸውን የአክሲዮን መምስረቻ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

...

ኢ.ኮ.ሥ.ኮ ከ11.8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) በ2016 የበጀት ዓመት ከ11.8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደሰበሰበ ገለጸ፡፡

 የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ነሃሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የተቋሙን ዓመታዊ ሥራ አፈጻጸም ለመገምገም በተጠራው ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት አ.ኮ.ሥ.ኮ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ11.8 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ችሏል፡፡

 ኮርፖሬሽኑ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን እና የተጠቀሰው የትርፍ መጠንም ለዓመቱ ከታቀደው ግብ ጋር ሲነጻጸር ከ100 በመቶ በላይ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

 ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኮርፖሬሽኑ ዓመታዊ አማካይ የቢ.ኤስ.ሲ ዕቅድ አፈጻጸም በመቶኛ ሲሰላ 95.4 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡

...

ኮርፖሬሽኑ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም እየተሳተፈ ነው

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን "ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063" በሚል መሪ ቃል

...

ኮርፖሬሽኑ ለማዕከሉ ተመጋቢዎች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (...) 120 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል አቅመ ደካማና አረጋዊያን

...

ኮርፖሬሽኑ ለማዕከሉ ተመጋቢዎች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ለ120 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል አቅመ ደካማና አረጋዊያን ተመጋቢዎች ለ2017 አዲስ ዓመት በዓል መዋያ ለእያንዳንዳቸው የ5ሺህ ብር በድምሩ የ600 ሺህ ብር ገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

ኮርፖሬሽኑ ላለፉት ሦስት ዓመታት እስከ 200 ለሚደርሱ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አቅመ ደካማና አረጋዊያን ነዋሪዎች በየቀኑ የምሣ፣ የሻይ እና ቡና አቅርቦት እንዲሁም ለተለያዩ በዓላት መዋያ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን የምገባ ማዕከሉ አስተባባሪ አቶ አብርሃም ሂርጶ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የተማሪዎች ምገባ ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ ገ/ፃዲቅ በድጋፍ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙ ሲሆን ዳይሬክተሩ ኮርፖሬሽኑ እያደረገ ላለው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፤ ለተመጋቢዎቹም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አዲሱ ዓመትም የሰላም፣ የፍቅር እና የብልፅግና ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

ተመጋቢዎች በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ እያደረገላቸው ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡