...

ኮርፖሬሽኑ ለ54 አቅመ ደካሞች የሚተላለፉ የጋራ የመኖሪያ ቤቶችን ግንባታ እያጠናቀቀ ነው

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9 ለሚኖሩ ባለዝቅተኛ ገቢ ነዋሪዎች 54 የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

 በኮርፖሬሽኑ የወረዳ 9 ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዳዊት አጥላው ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ለኮኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባልደረቦች እንደተናገሩት ግንባታውን ከታቀደለት ጊዜ በፊት ለመጨረስ በመፋጠን ላይ የሚገኘው ፕሮጀክት የባለ አራት ወለል ህንጻን፣ አንድ ወርክሾፕን እና የ14 ሱቆችን ግንባታ የሚያጠቃልል ነው፡፡

 በወረዳው ለሚገኙ ለዋሪዎች እየተገነቡ የሚገኑት የመኖሪያ ቤቶች 24 ስቲዲዮዎችን፣ 10 ባለ አንድ መኝታ ክፍል እና 20 ባለ ሁለት መኝታ ክፍል ቤቶችን እንደሚያካትት ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

 የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከ328.4 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን የኮንትራት ዋጋ በጥር ወር 2016 ዓ.ም ግንባታቸው የተጀመሩት የጋራ የመኖሪያ ቤቶች በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

...

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ መሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ አፈጻጸም 95 በመቶ ደረሰ

ቀን: Nov 30, -1

ከ515.4 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የተከለሰ የኮንትራት ዋጋ እየተገነባ የሚገኘው የሰመራ ዩኒቨርሲቲ መሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ አፈጻጸም እስከ ያዝነው የበጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ማብቂያ ድረስ 95 በመቶ እንደነበር ተገለጸ፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ መሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖችን ግንባታ፣ የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታ፣ የመንገድ መብራት ተከላ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦዎች ቀበራ እና ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን እንደሚያጠቃልል ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ተቋራጭነት እና በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አማካሪነት እየተካሄደ የሚገኘው የግንባታ ሥራ በግንቦት ወር 2011 ዓ.ም እንደተጀመረ ይታወቃል፡፡   

...

የኮርፖሬሽኑ የአትሌቲክስ ክለብ አባላት ድል አስመዘገቡ

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትሌቲክስ ክለብ አባላት የሆኑት አትሌት ፀሀይነሽ ከፋለ እና

...

የኮርፖሬሽኑ አትሌት በሳምንት ውስጥ ሁለት ሜዳሊያዎችን አገኘች

ቀን: Nov 30, -1

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ስፖርት ክለብ አትሌት በሀገረ ቻይና በተካሄዱ ሁለት የሩጫ ውድድሮች የወርቅ እና የብር ሜዳሊያዎችን አገኘች፡፡

ክለቡ ሚያዚያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ለኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በላከው መረጃ መሰረት ዘውዲቱ አሸናፊ የተባለች አትሌት በ21 ኪሎ ሜትር (ግማሽ ማራቶን) እና የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድሮች በቅደም ተከተል 1ኛ እና 2ኛ በመውጣት የወርቅ እና የብር ሜዳሊያዎችን ከገንዘብ ሽልማት ጋር አግኝታለች፡፡

ሁለቱ ውድድሮች በአንድ ሳምንት ውስጥ ማለትም ሚያዚያ 06 ቀን 2016 ዓ.ም እና ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም የተደረጉ ሲሆን አትሌቷ በሁለቱም ውድድሮች እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማምጣቷ ኮርፖሬሽኑን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስጠራት ችላለች፡፡

...

በዶ/ር ፍጹም አሰፋ የተመራ የሱፐርቪዥን ቡድን ኮርፖሬሽኑን ጎበኘ

ቀን: Nov 30, -1

በኢ... የዕቅድ እና ልማት ሚኒስትር / ፍጹም አሰፋ የተመራ

...

ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ እየተሳተፈ ነው

ቀን: Nov 30, -1

ኮርፖሬሽኑ ለእይታ ያቀረባቸው የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግብአት ምርቶች በጎብኚዎች እየታዩ ነው።

ኤክስፖው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር / አብይ